አገልግሎቶቻችን

የአባልነት መስፈርት

አባል መሆን የሚችለው ማን ነው?

- የልጆች ቁጠባ በዎላጆቻቸው አማካኝነት የሚቀጠብላቸው ይሆናል፡፡
- በማኅበሩ ውስጥ በተለያዩ ኮሚቴዎች ሲመረጥ ያለ ክፍያ ለማገልገል ፈቃደኛ የሆነ፤
- ከአባላት ጋር ተመሳሳይ ፍላጐትና ዓላማ ያለው
- የኅብረት ሥራ ማህበሩ ዕውቅና ባገኘባቸው የስራ ክልል ሆነው የነዋሪነት መታወቂያ እና ፈይዳ (በሔራዊ መታወቂያ) ያለው ወይም ያላት መሆን ይኖርበታል፡፡

ቁጠባ

01.

መደበኛ ቁጠባ

ማንኛውም የኅብረት ሥራ ማኅበሩ አባል የሆነ የማህበሩን መነሻ ወይም ዝቅተኛ መደበኛ ቁጠባ ብር 500 ሳያቋርጥ በየወሩ መቆጠብ ይኖርበታል፡፡ አንድ አባል የቆጠበውን መደበኛ ቁጠባ ማውጣት የሚችለው ከአባልነት ሲለቅ ብቻ ነው፡፡

አንድ አባል የንግድ ሥራ ለመጀመርም ሆነ ለማሻሻል ቢፈልግ ለስድስት ወር በተከታታይ ሳያቆርጥ የሚወስደውን ብድር መጠን 25% (በመቶ) የቆጠበ እና 5% እጣ የገዛ አባል የንግድ ሥራ መጀመሪያ ወይም ማሻሻያ ብድር ለመጠየቅ ብቁ ይሆናል፡፡

02.

የፍቃደኝነት ቁጠባ

አንድ አባል ከመደበኛ ቁጠባ በተጨማሪ የፍላጎት ቁጠባ መቆጠብ ይችላል፡፡ ይህንንም ቁጠባ በማንኛውም ጊዜ ወጪ ማድረግ ይችላል፡፡

03.

የግዜ ገደብ ቁጠባ

አንድ አባል በግዜ ገደብ ሲቆጥብ ለቆጠበው ቁጠባ በዓመት 10 በመቶ የተቀማጭ ወለድ ይታሰብለታል፡፡ 

04.

ለቤት ግዥ ቁጠባ

አንድ አባል ለተከታታይ ስድስት ወራት ከብድር ጥያቄው 35% የቆጠበ እና 5% እጣ የገዛ አባል የቤት ግዥ ብድር ለመጠየቅ ብቁ ይሆናል፡፡

05.

ለመኪና ግዥቁጠባ

አንድ አባል ለተከታታይ ስድስት ወራት ከብድር ጥያቄው 30% የቆጠበ እና 5% እጣ የገዛ አባል የመኪና ግዥ ብድር ለመጠየቅ ብቁ ይሆናል፡፡

06.

የሴቶችና ወጣቶች ቁጠባ

የሴቶችና ወጣቶች ቁጠባ ወደፊት የተሻለ ህይወት እንዲመሩ አዋጪ በሆነ የገቢ ማስገኛ ስራዎች ላይ እንዲሰማሩ ከስልጠናና የማማከር አገልግሎት ጋር ብድር ይመቻቻል፡፡

07.

የወል ቁጠባ /የትምህርት፣የክብረ በዓላት፣የህክምና/

አንድ አባል ከመደበኛ ቁጠባ በተጨማሪ የትምህርት፣የክብረ በዓላት፣የህክምና/ ቁጠባ መቆጠብ ይችላል፡፡ ይህንንም የወል ቁጠባ በታቀደለት ጊዜ ወጪ ማድረግ መጠቀም ይችላል፡፡

08.

የልጆች ቁጠባ

የማኅበረሰቡ የመቆጠብ ልምድ እንዲያድግ ማንኛውም ሰው በኅብረት ሥራ ማህበር ውስጥ እንዲገባና እና ልጆቹንም አባል እንዲያደርግ ያመቻቻል፡፡በተጨማሪም ወላጆቻቸውን ላጡ ህፃናት ከወለድ ነፃ ብድር ያመቻቻል፡፡

09.

የቁጠባ ወለድ

አንድ አባል ለቆጠበው መደበኛ ቁጠባ በዓመት 7% (በመቶ) የተቀማጭ ወለድ ይታሰብለታል፡፡ 

ብድር

ብድር

በማህበሩ ዘንድ የተጠራቀመውን የአባላት ገንዘብ ያለአድሎና ልዩነት ለአባላቱ በብድር መልክ መስጠትና ተመልሶ መከፈሉንም ማረጋገጥ ሲሆን ይህም የሚከተሉትን መሰረተ ሀሳቦች በመከተል አስፈላጊ ይሆናል፡፡

  • የአባሉ ፍላጎት፣
  • የአባሉ የገንዘብ አጠቃቀም ልምድ
  • አባሉ የሚያቀርበው የዋስትና ብቃት
  • የአባሉ የመክፈል አቅምና ችሎታ
  • የአባሉ የቁጠባና ዕጣ መጠን
  • የማህበሩ የገንዘብ አቅም የመሳሰሉትን የሚያጠቃልል ይሆናል፡፡

ብድር ለማግኘት የሚያስፈልጉ መስፈርቶች

  • የብድር ጠያቂዉ የማኅበሩ አባል መሆን አለበት
  • አባል ሆኖ ስድስት ወራት መቆየት ይኖርበታል፡፡
  • እንደሚበደረው የገንዘብ መጠን በማኅበሩ የተቀመጠውን የቆይታ ጊዜ ማሟላት አለበት
  • በሚጠይቀው የገንዘብ መጠን ልክ በማኅበሩ የተቀመጠውን ዕጣ (ሼር) የገዛ እና ቁጠባውን ቀድሞ ወይም ሳይቆራረጥ ብድሩን እስኪጠይቅ ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ የቆጠበ መሆን አለበት፡፡
  • የገቢ ማስረጃ እና ዋስትና ማቅረብ የሚችል
  • የታደሰ መታወቂያ ካርድ እና ብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) ማቅረብ የሚችል
  • የተበዳሪውም ሆነ የዋሱ የጋብቻ ሰርተፊኬት ባለትዳር ካልሆኑ ያላገባ የምስክር ወረቀት ጊዜው ያላለፈበት ሰርተፊኬት ወይም ፍቺ ከሆነ ከፈርድ ቤት የፊቺ ማስረጃ ማምጣት የሚችል፡፡

የብድር ዓይነቶች

  • መደበኛ ብድር
  • የቤት ግዥ ብድር
  • የመኪና ግዥ ብድር

መደበኛ ብድር

አንድ አባል የንግድ ሥራ ለማስፋፋትና ለማሻሻል ቢፈልግ ለስድስት ወር በተከታታይ ሳያቆርጥ የሚወስደውን ብድር መጠን 25% (በመቶ) የቆጠበ እና 5% እጣ የገዛ አባል መሆን ይኖርበታል፡፡ መበደር የሚችለው እስከ ብር 1,200,000 (አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሺ) ድረስ ነው።

የቤት ግዥ ብድር

አንድ አባል ለተከታታይ ስድስት ወራት ከብድር ጥያቄው 35% (በመቶ) የቆጠበ እና 5% እጣ የገዛ አባል ቤት ለመግዛት፣ ለመገንባት ወይም ለእድሳት ይበደራል። አንድ አባል እስከ ብር 3,000,000.00 (ሦስት ሚሊዮን) ለቤት ብድር መበደር ይቻላል።

የመኪና ግዥ ብድር

አንድ አባል ለተከታታይ ስድስት ወራት ከብድር ጥያቄው 30% (በመቶ) የቆጠበ እና 5% እጣ የገዛ አባል መኪና ለመግዛት ይበደራል። አንድ አባል መኪና ለመግዛት እስከ ብር 2,500,000 (ሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺ) መበደር ይቻላል።

የብድር አከፋፈል ሁኔታ

  • ከብር 10,000 እና ከዚህ በታች ለሚበደሩ በ12 (አስራ ሁለት) ወራት ውስጥ ከፍሎ መጠናቀቅ ይኖርበታል፡፡
  • ከ10,001 ብር እስከ 50,000 /ሃምሳ ሺ ብር በ24 ወራት ውስጥ ከፍሎ መጠናቀቅ ይኖርበታል፡፡
  • ከ50,001 ብር እስከ 100,000 /አንድ ሺ ብር ለሚበደሩ 36 ወራት ውስጥ ከፍሎ መጠናቀቅ ይኖርበታል፡፡
  • ከ100,001 ብር እስከ 200,000 /ሁለት መቶ ሺ ብር ለሚበደሩ በ48 ወራት ውስጥ ተከፍሎ መጠናቀቅ ይኖርበታል፡፡
  • ከ200,001 እስከ 300,000 /ሦስት መቶ ሺ ብድር ለሚበደሩ በ60 ወራት ውስጥ ተከፍሎ መጠናቀቅ ይኖርበታል፡፡
  • ከ300,001 እስከ 600,000 /ስድስት መቶ ሺ / ብድር ለሚወስዱ በ72 ወራት ውስጥ ተከፍሎ መጠናቀቅ አለበት፡፡
  • ከ600,001 እስከ 900,000 /ዘጠኝ መቶ ሺ / ብድር ለሚወስዱ በ84 ወራት ውስጥ ተከፍሎ መጠናቀቅ ይኖርበታል፡፡
  • ከ900,001 እስከ 1,200,000 /አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሺ / ብድር ለሚወስዱ በ96 ወራት ውስጥ ተከፍሎ መጠናቀቅ ይኖርበታል፡፡
  • ከ1,200,001 እስከ 3,000,000 /ሦስት ሚሊዮን / ብድር ለሚወስዱ በ120 ወራት ውስጥ ተከፍሎ መጠናቀቅ ይኖርበታል፡፡
  • ተበዳሪው አባል የብድር ክፍያ የሚጀመርበት ቀንና ወር በግልጽ አውቆ ክፍያውን ተግባራዊ ማድረግ ግዴታው ሲሆን ይህም በብድር ውሉ ላይ መጠቀስ ይኖርበታል፡፡
  • ብድር ከወሰዱ በኋላ ክፍያ ለመጀመር የአንድ ወር የእፎይታ ጊዜ ይኖረዋል፡፡

የወለድ አከፋፈል

  • ማህበሩ ለአባላቱ ለሚሰጠው የብድር አገልግሎት የወለድ ምጣኔ 12% (መቶኛ) ሲሆን አከፋፈሉም የአመቱን ወለድ ለ 12 ወራት በማካፈል በየወሩ ወለድ ይከፈላል፡፡
  • ማንኛውም አባል ከማህበሩ ለተበደረው ገንዘብ በየዓመቱ በቀሪው ገንዘብ ላይ የሚታሰብ 12% ወለድ ይከፈላል፡፡

የብድር ዋስትና

በደመወዝ ዋስትና የሚሰጥ ብድር

በደመወዝ ዋስትና የሚሰጥ ብድር

የሚያቀርበው የተበዳሪም ሆነ የዋስ የዋስትና ደብዳቤ ከመንግስት መስሪያ ቤት እና ከታወቀ የግል ድርጅት መሆን አለበት፡፡ ከሚሰራበት መስሪያ ቤት የደመወዙ መጠን፤ ቋሚ ሰራተኛ መሆኑንና ጡረታ ለመውጣት የቀራቸው ጊዜ፤ ከሌላ ተቋም ብድር የወሰደ መሆንና አለመሆኑን፣ ተበዳሪውም ሆነ ዋሱ መስራ ቤቱን ቢለቁ በቅድሚያ የሚያሳዉቁ መሆኑን እና የስራ ግብር ከፋይ መሆኑን የሚገልጽ እና የግል ድርጀት ከሆነ ድርጀቱ 10 ዓመት በላይ የቆየ እና ሰራተኛው የስድስት ወር ፔሮል ማስረጃ ማቅረብ አለበት፤ የዋሱ ሚስት/ባል መፈረም አለበት/ባት፡፡በዚህ መሰረት፡

የመኪና ዋስትና በመጠቀም የሚሰጥ ብድር

ü  የሚሰጠው ብድር መኪናው ኢንሹራንስ ከገመተው እና ከተገዛበት ዋጋ 85% በላይ መሆን የለበትም፡፡

 

  • በዋስትና የሚያዘው መኪና ከተመረተ/በሊብሬው መሰረት/ 20 አመት ያልበለጠው መሆን አለበት፡፡

 

  • መኪናው ተፈትሾ ለብድር ዋስትናው ብቁ መሆን አለበት

 

  • ሙሉ ኢንሹራንስ የገባና እንዳይሸጥ፣ እናዳይለወጥ እንዲሁም ለሶስተኛ ወገን አንዳይሰጥ የታገደ መሆን አለበት፡፡

 

የቤት ዋስትና በመጠቀም የሚሰጥ ብድር

  • ቤቱ ለብድሩ ተመጣጣኝ ዋስትና ሊሆን ይገባላ
  • ቤቱ ካርታና ፕላን ሊኖረው ይገባል ግንባታውም በፕላኑ መሰረት መሰራት ይኖርበታል፤
  • ቤቱ ዲጂታል የሆነ ካርታ ያለውና እንዳይሸጥ፣ እናዳይለወጥ እንዲሁም ለሶስተኛ ወገን አንዳይሰጥ የታገደ መሆን አለበት፡፡.

የስልጠናና ማማከር አገልግሎት

     ​ብዙኃን የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር ለአባላቱ የተለያዩ የስልጠና እና የማማከር አገልግሎት በመስጠት የሰዎችን የገንዘብ አጠቃቀም ባህል ለማሳደግ እና ተቋማዊ አሰራርን ለማጠናከር ወሳኝ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።

1. የስልጠና አገልግሎቶች (Training Services)

​ብዙኃን የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር ለአባላቱ የተለያዩ የስልጠና እና የማማከር አገልግሎት በመስጠት የሰዎችን የገንዘብ አጠቃቀም ባህል ለማሳደግ እና ተቋማዊ አሰራርን ለማጠናከር ወሳኝ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።

​1. የስልጠና አገልግሎቶች (Training Services)

​እነዚህ ስልጠናዎች አባላት በገንዘብ ነክ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን እውቀት ለማሳደግ እና ተቋሙን በብቃት ለመምራት የሚሰጡ ናቸው።

​ሀ. ለአባላትና ለደንበኞች የሚሰጡ ስልጠናዎች

የመግቢያ (ኦረንቴሽን) ስልጠና፦ አዳዲስ አባላት ስለ ማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ፣ መብትና ግዴታዎች፣ እንዲሁም ስለ ቁጠባና ብድር መመሪያዎች በቂ እውቀት እንዲያገኙ ይደረጋል።

የመሰረታዊ ገንዘብ አያያዝ ስልጠና፦ የግል ወይም የቤተሰብ በጀት እንዴት እንደሚታቀድ፣ አላስፈላጊ ወጪዎችን እንዴት መቀነስ እንደሚቻል እና የቁጠባ ባህልን እንዴት ማሳደግ እንደሚቻል የሚያስተምር ስልጠና ነው።

የስራ ፈጠራ እና ቢዝነስ አመራር ስልጠና፦ አባላት የሚወስዱትን ብድር ባልባሌ ነገር ላይ እንዳያባክኑት፣ አዳዲስ የቢዝነስ ሃሳቦችን እንዴት ማመንጨትና ማስተዳደር እንዳለባቸው ግንዛቤ ይሰጣል።

የብድር አጠቃቀምና አመለባበስ ስልጠና፦ የተበደሩትን ገንዘብ ለታለመለት አላማ ማዋልና ብድርን በወቅቱ የመመለስን ጥቅም (የብድር ዲሲፕሊን) የሚያስገነዝብ ስልጠና ነው።

. ለስራ አስፈፃሚዎችና ለሰራተኞች የሚሰጡ ስልጠናዎች

የአመራርና አስተዳደር ስልጠና፦ የማህበሩ የስራ አመራር ቦርድ እና የተለያዩ ኮሚቴዎች (ለምሳሌ፡ የብድር ኮሚቴ፣ የቁጥጥር ኮሚቴ) ስራቸውን በግልፅነትና በተጠያቂነት መወጣት እንዲችሉ የሚሰጥ ስልጠና ነው።

የሂሳብ አያያዝና ሪፖርት አቀራረብ ስልጠና፦ የማህበሩ ሰራተኞች እና የሂሳብ ባለሙያዎች ዘመናዊ የሂሳብ አያያዝ ዘዴዎችን እና የፋይናንስ ሶፍትዌሮችን ተጠቅመው ትክክለኛ ሪፖርት ማዘጋጀት እንዲችሉ የሚሰጥ ስልጠና ነው።

2. የማማከር አገልግሎቶች (Advisory & Counseling Services)

​ማማከር በአብዛኛው በግል ወይም በቡድን ፍላጎት ላይ ተመስርቶ ችግሮችን ለመፍታት እና የተሻለ ውሳኔ ለመወሰን የሚሰጥ ድጋፍ ነው።

የፋይናንስ እና የኢንቨስትመንት ምክር፦ አባላት ያላቸውን ቁጠባ ወይም የወሰዱትን ብድር በምን አይነት አትራፊ የስራ ዘርፍ ላይ ቢያውሉት የተሻለ እንደሆነ የገበያ ሁኔታን ያገናዘበ ምክር መስጠት።

የብድር ማመልከቻ እና የቢዝነስ እቅድ (Business Plan)ማማከር፦ አባላት ብድር ከመውሰዳቸው በፊት የሚሰሩትን ስራ አቅራጭ እቅድ (ፕሮፖዛል) እንዴት ማዘጋጀት እንዳለባቸውና የገንዘብ ፍሰታቸውን (Cash Flow) እንዴት ማጋጠም እንደሚችሉ ማገዝ።

የብድር ማቃለልና የምክር አገልግሎት (Debt Counseling) አባላት በስራ መበላሸት ወይም በተለያዩ ምክንያቶች ብድር መመለስ ሲያቅታቸው፣ ካሉበት የዕዳ ጫና የሚወጡበትን ስትራቴጂ መንደፍ እና የብድር ማራዘሚያ (Rescheduling) ሁኔታዎችን ማማከር።

የአደጋ ስጋት አስተዳደር ምክር (Risk Management) በስራ ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ኪሳራዎችን አስቀድሞ እንዴት መከላከል እንደሚቻል እና የቁጠባ ዋስትናዎችን በተመለከተ የሚሰጥ ምክር።

ባጭሩ፦ እነዚህ አገልግሎቶች አባላት የተሻለ የገቢ ምንጭ እንዲፈጥሩና ህይወታቸውን እንዲለውጡ የሚያግዙ ሲሆን፣ ለተቋሙ ደግሞ የማይመለስ ብድር (Non-performing loans) እንዳይበራከትና ተቋማዊ ጥንካሬ እንዲኖር ያደርጋሉ።

Scroll to Top