ስለ እኛ
ራዕይ
በአዲስ አበባ ከተማ ከሚገኙ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ ማህበራት ውስጥ ግንባር ቀደም ተመራጭ እና እጅግ የተከበረ የቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ ማኅበር ሆኖ ማየት፤
ተልዕኮ
አባላትን በተለያዩ የቁጠባ ዘርፎች በማሳተፍ ገንዘብ በማበደርና ካፒታል በማፍራት በወልም ሆነ በተናጠል የሀብት ባለቤት እንዲሆኑ ማድረግ፤
ግብ
በአባላት እጅ ተበታትነው የሚገኙትን ሀብቶች በቁጠባ በማሰባሰብ አዋጭ በሆነ የንግድ ወይም ሌላ ገቢ ማስገኛ ሥራ ውስጥ በማሳተፍ የተሻለ ገቢ እንዲያገኙ ማድረግ፤
ስለ እኛ
የሥጋ ደዌ ተጠቂዎችና ሌሎች አካል ጉዳተኞች በሚደርስባቸው ከፍተኛ አድሎና የመገለል ጫና ምክንያት ከፍተኛ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች እንደሚደርስባቸው ይታወቃል፡፡ ከሚደርስባቸው ጫና በትግላቸው ለመላቀቅ የወሰኑ 51 ወንድ እና 24 ሴት በጠቅላላው 75 አካል ጉዳተኞች በመሰባሰብ ባዋጡት 11,000.00 /አስራ አንድ ሺህ/ ብር እና ከጀርመን ሥጋ ደዌ እና ቲቢ እርዳታ ማኅበር በተገኘ 25,000/ሃያ አምስት ሺህ/ብር የገንዘብ ድጋፍ በድምሩ 36,000.00/ ሰላሳ ስድስት ሺህ / ብር በመያዝ ሐምሌ 11 ቀን 2000 ዓ.ም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የአካል ጉዳተኞች የብድርና ቁጠባ አገልግሎት የሚሰጥ ማሕበር መሠረቱ፡
የጀርመን ሥጋ ደዌ እና ቲቢ እርዳታ ማኅበር ለመነሻ ካፒታል በልግስና ከሰጠው የ25 ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ በተጨማሪ ለቢሮ ግንባታና ለቁሳቁስ ማሟያ ተጨማሪ የ31,500 ብር ድጋፍ ማድረጉ ይታወቃል፡፡በወቅቱ ለተመሠረተው ማሕበር የተሰጠው ሥያሜ “የአዲስ አበባ ክልል ሥጋ ደዌ ተጠቂዎችና አካል ጉዳተኞች የገንዘብ ቁጠባና ብድር ሃላፊነቱ የተወሰነ የህብረት ሥራ ማህበር” የሚል ነበር፡፡
ቆይቶ ግን በአካል ጉዳተኞች ሥም ብቻ መሰየሙ በአካባቢው በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኘውን ብዙሃን ማህበረሰብ በበቂ ሁኔታ ለማሳተፍ አዳጋች በመሆኑ ስያሜው ቢቀየር የሚል ሀሳብ ቀርቦ ተቀባይነት በማግኘቱ ከምሥረታው ሰባት ዓመታት በኋላ የካቲት 30 ቀን 2007 ዓም “ብዙኃን የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የህብረት ሥራ ማኅበር” ተብሎ በአዲስ ስያሜ እንደገና ተደራጀ፡፡ በዚያን ወቅት የአባላቱ ቁጥር 534 ደርሶ ነበር፡፡
በምሥረታው ወቅት ለአንድ አባል 3,000 ብር ብቻ የማበደር አቅም የነበረው ማኅበር በአሁኑ ወቅት ከፍተኛውን የብድር ጣሪያ እስከ 3,000,000 ብር ለማበደር የሚያስችል አቅም አጎልብቷል፡፡ በመጀመሪያዎቹ የማኅበሩ የምሥረታ ዓመታት በዓመት ለብድር የሚመደበው የገንዘብ መጠን ከ36,000 ብር ያልበለጠ ሲሆን በ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት140,000,000 (አንድ መቶ አርባ ሚሊዮን ብር) ለማብደር ተችሏል፡፡
በአሁኑ ወቅት በአባልነት ወንድ 1,577(55.25%) ሴቶች 1,277 (44.75%) በድምሩ 2,854 አባላት ተመዝግበው ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ የቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ ማሕበሩ በአዋጅ 985/2009 የተቋቋመ በአነስተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ብዙዎችን ሕይወት የለወጠ ፣ አገልግሎቱንም ከጊዜ ወደ ጊዜ በማሻሻልና ተደራሽነቱንም በማስፋት ላይ የሚገኝ ሲሆን በተመሳሳይ የአገልግሎት ዘርፍ ከተሰማሩ ሌሎች ተቋማት ጋር በመወዳዳር የአባላቱን ቁጥር ይበልጥ በማሳደግ ጊዜውን የዋጀ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ብቁ ቁመና ላይ ይገኛል፡፡
የማሕበሩ የሥራ አመራር ቦርድ አባላት
አቶ ኣዳነ ዋለ
/ሰብሳቢ/
Red Kidney Beans
አቶ ይርጋለም ኃይሌ
ም/ሰብሳቢ/
አቶ በውቀቱ አስማማው
/ፀሐፊ/
ወ/ሪት ሀብታም ጆቴ
/ሂሳብ ሹም/
መ/ርት ይታይሽ እስተመች
/አባል /
ወ/ሪት አባይነሽ ታከለ
/ገንዘብ ያዥ/
